Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችንና ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር ሁሉን አቀፍ ዝግጅ | ትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችንና ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር ሁሉን አቀፍ ዝግጅት እየተደረገ ነው-
.............................................

መጋቢት 29/2015ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር)፦ በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎችን እና አጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር የስርዓተ ትምህርትና የመምህራን ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶችና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች በክልሉ ትምህርት ማስጀመር የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።

መንግስትና ህወሃት በፕሪቶሪያ የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ከማቅረብ ጀምሮ የክልሉን ህዝብ በዘላቂነት ማቋቋም የሚያስችሉ የመልሶ ግንባታና መሰረታዊ አገልግሎቶች እየተሰጡ ነው።

መንግስት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም፣ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው ወደ መደበኛ ህይወት እንዲመለሱ፣ መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ፣ እንዲሁም ትምህርት እንዲጀመር የሰላም ስምምነቱን እየተገበረ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በውይይቱ ላይ እንዳሉት፣ በግጭቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የዩኒቨርሲቲዎችና አጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው።

በዚህም የትምህርት ተቋማት የደረሰባቸውን የጉዳት መጠን በማጥናት ትምህርት ለመጀመር የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ለይተን ቅድመ ዝግጅት ጀምረናል ብለዋል።