Get Mystery Box with random crypto!

ከመጽሀፍ ገጾች..... ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሶሶተኛውን መፃፋቸውን : | ትምህርት ሚኒስቴር

ከመጽሀፍ ገጾች.....

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሶሶተኛውን መፃፋቸውን : የመደመር ትውልድ ማስመረቃቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ መጽሃፍ የትምህርት ጉዳይ አስኳላ እና አስኳል በሚለው ርዕስ ሥር ቀርቧል፡፡ አስኳላ እና አስኳል በሚለው ክፍል የተወሰዱ ገጾች እነሆ

.

"ዘመናዊው ትምህርት ከነባሩ ተፋትቶ መጀመሩ ሶስት ችግሮችን አመጣ። በትምህርትና በዕውቀት ዘርፍ ከዚያ በፊት የተሰራውን ሁሉ እንዳልተሠራ ቆጠረው። ከመሠረቱ የተነቀለ፤ ሀገሩን የማያውቅ ትውልድ ተፈጠረ። በአውሮፓ ነባራዊ ሁኔታ የተቃኘ፤ ለአውሮፓውያን የተቀረፀን ዕውቀት የሚያነበንብ ትውልድ ተፈጠረ። ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ በመሆኑ፤ የኢትዮጵያን ችግር በአውሮፓ መነጽር በመመልከት፤ ለብዙ ችግሮች መፈጠር ምክንያት ሆኗል"
(ዐብይ አህመድ :- የመደመር ትውልድ 2015 ገጽ 227)