Get Mystery Box with random crypto!

በዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ለሴቶች፣ ልዩ ፍላጎት ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ምቹ ሁኔታ ለ | ትምህርት ሚኒስቴር

በዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ለሴቶች፣ ልዩ ፍላጎት ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡፡
……………………………………………

መጋቢት 28/2015ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር) ፡ትምህርት ሚኒስቴር ለሴቶች፣ ልዩ ፍላጎት ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ወቅት ምቹ ሁኔታ መፍጠር በሚቻልበት ሂደት ላይ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ኃላፊዎች ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ የትምህርት ሚኒስቴር የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይና አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ የትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ያለውን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እየሰራ እንዳለ ጠቅሰው ከዚህ ውስጥ አንደኛው የመውጫ ፈተና ነው ብለዋል፡፡

በመውጫ ፈተናው ከስርዓተ ፆታ አንፃር እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውና ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ ተመራቂ ተማሪዎችን እኩል እንዲሳተፉ ምቹ የፈተና አካባቢ በመፍጠር ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚጠበቅም ገልፀዋል።

በዝግጅት ምዕራፍ፣ ከመፈተኛ ቦታዎች፣ ከመፈተኛ ቁሳቁሶች እንዲሁም በፈተና ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ የሰርዓተ ፆታ ጉዳዮች ለይቶ ከወዲሁ መፍታት እንደሚገባም ተገልጿል።

ሙሉ መረጃውን

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et

ይከታተሉ
---------