Get Mystery Box with random crypto!

ያለፈው የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጠንክረን እንድንሰራ አድርጎናል ሲሉ የ2015ዓ | ትምህርት ሚኒስቴር

ያለፈው የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጠንክረን እንድንሰራ አድርጎናል ሲሉ የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ገለጹ፡፡
---------------------------------------------
መጋቢት 22/2015 ዓም .(የትምህርት ሚኒስቴር) የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጠንክረን እንድንሰራ አድርጎናል ሲሉ የጣና ሀይቅ አጠ/ከፍ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ተናገሩ።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጥበት አዲሱ የፈተና ስርዓት ተማሪው በሰራው ልክ የሚመዘንበት በመሆኑ ጠንክረን እንድንሰራ አድርጎናልም ብለዋል።

የጣና ሀይቅ አጠ/ከፍ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት ም/ር/መምህር አቶ ጸጋዬ ተፈራ ከዚህ ቀደም የነበረው የፈተና ስርዓት ለኩረጃ የተጋለጠ እና ተማሪዎች በቂ ዝግጅት የማያደርጉበት እንደነበረ ገልፀዋል።

አሁን ላይ ተማሪው በሰራው ልክ የሰራውን የሚያገኝበት የፈተና ስርዓት በመዘርጋቱ ለተማሪዎችም ይሁኑ ለመምህራን ጠንክረን እንድንሰራ አድርጎናል ሲሉም ተናግረዋል።
ሙሉ ዜናውን

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et

ይከታተሉ
---------