Get Mystery Box with random crypto!

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቆጮን በዘመናዊ መንገድ ማምረት የሚስችል ቴክኖሎጂን በስፋት ለህብረተሰቡ ለ | ትምህርት ሚኒስቴር

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቆጮን በዘመናዊ መንገድ ማምረት የሚስችል ቴክኖሎጂን በስፋት ለህብረተሰቡ ለማድረስ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
-------------------------------------------------
መጋቢት 12/2015ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንሰትን በዘመናዊ መንገድ በማምረት ለምግብነት ለማዋል የሚያስችል ቴክኖሎጂን በማልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው የእንሰት ፕሮጀክት ተመራማሪና አስተባባሪ አዲሱ ፈቃዱ( ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

እንሰት በባህላዊ መንገድ ሲዘጋጅ ብዙ ተግዳቶች ያሉበት፣ የመብላላት ሂደቱ ረጅም ጊዜ የሚፍጅና ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ይህንን የሚቀይር ሳይንሳዊ ሂደቱን የተከተለ የተሻለ ቴክኖሎጂ በመፍጠር አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም በቀላሉ እንሰትን መፋቅ የሚያስችል የእንሰት መፋቂያ ማሽን በመስራት የቆጮውን ጥራት ከመጠበቅ ባለፈ የእናቶችን ድካም በከፍተኛ መጠን ማስቀረት የሚያሰችል ቴክኖሎጂ መፍጠር መቻሉን ተመራማሪው ገልፀዋል፡፡

አዲሱ ቴክኖሎጂ ብክነትን ከመቀነስ ባሻገር አርሶ አደሩ ድረስ በመሞከረና ውጤታማነቱን በማረጋገጥ አርሶ አደሩ ጥቅም ላይ እንዲያውለው መደረጉንም ዶ/ር አዲሱ አብራርተዋል፡፡


ሙሉ ዜናው
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0DXNH36xxwsfGpCJbcdGctnQeLdn6gwcg8U9ATqBrSGqEu5oVE1hCzAujR4hkLB5yl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz