Get Mystery Box with random crypto!

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ኃይል ልማት ለገጠር ሥራ ፈጠራ በተሰኘ ፕሮጀክት የማህበረሰብ አገል | ትምህርት ሚኒስቴር

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ኃይል ልማት ለገጠር ሥራ ፈጠራ በተሰኘ ፕሮጀክት የማህበረሰብ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
======================

መጋቢት 10/2015ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ኃይል ልማት ለገጠር ሥራ ፈጠራ በተሰኘ በምርምር በታገዘ ፕሮጀክት ውጤታማና ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተስፋየ ሸፈራው (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣በሶፍትዌር ኢንጅነሪኒግ፣በግብርና እና በሌሎችም ዘርፎች በአሁኑ ወቅት ማህበረሰቡ እየተገለገለባቸው ያሉ በርካታ የምርምር ውጤቶችን ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ተስፋየ ዩኒቨርስቲው ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት አቅም ያለው መሆኑን ገልፀው ይህንን ለማድረግም ከህብረተሰቡ፣ ከባለሀብቶች እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር በቅርበት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲው የዘላቂ ኃይል ልማት ለገጠር ሥራ ፈጠራ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ነገሰ ያዩ የዘላቂ ኃይል ልማት ለገጠር ሥራ ፈጠራ ፕሮጀክት ዩኒቨርሲቲው ውጤታማ ከሆነባቸው በምርምር ታግዘው ከሚሠሩ በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ሙሉ መረጃው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02CpC9wmcTzwcqzQJuishKThaPM8x9F5UnPmETRXUUtLszwjKdqtbgKjyWYW3Tbs8Fl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz