Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ተማሪዎች በሚፈልጉት የትምህርት መስክ በቂ እውቀት እን | ትምህርት ሚኒስቴር

አዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ተማሪዎች በሚፈልጉት የትምህርት መስክ በቂ እውቀት እንዲይዙ እድል የሚፈጥር እንደሆነ ተማሪዎች ተናገሩ
-----------------------------------

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ሰርዓተ-ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲሱን የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ሙሉ ለሙሉ እንዲሁም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ደግሞ የሙከራ ትግበራ ላይ ይገኛል።

አዲሱ ሰርዓተ-ትምህርት ሀገር በቀል እውቀትን በማካተት ከንድፈ ሃሳብ በተጨማሪ ለተግባር ትምህርት ትኩረት በመስጠት እና የግብረ-ገብ ትምህርትን በማካተት እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሆኖ 21ኛው ክፍለ ዘመን የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት ማስጨበጥ በሚችል መልኩ ተዘጋጅቶ ወደ ሰራ ተገብቷል።

በአሁን ሰዓት በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል በሙከራ ላይ ያለውን ይህን ስርዓተ-ትምህርት አስመልክቶ የዳግማዊ ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሃሳባችውን አካፍለውናል።

በትምህርት ቤቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ቅድስት ወንደሰን አዲሱ ስርዓተ-ትምህርት ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር ተግባር ተኮር በመሆኑ ተማሪዎች ሙሉ እውቀት እንዲይዙ የሚያስችል መሆኑን ገልፃለች። አዲሱ ስርዓተ-ትምህርት ተማሪዎች በሚፈልጉት የትምህርት መስክ ላይ በቂ እውቀት እንዲይዙ እድል የሚፈጥርም ነው ስትል ትናገራለች።
ሙሉ ዜናው
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02GYRmbM4ventmX6FkLTqoaPmXv9g3Q2FB2fpwTMkTbjjmHrXC4iw11pVqc7ivDty7l&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz