Get Mystery Box with random crypto!

#ማስታወቂያ በ2014 ዓም. 12ኛ ክፍል የላቀ ዉጤት አምጥታችሁ የዉጪ ሀገር የትምህርት እድል/S | ትምህርት ሚኒስቴር

#ማስታወቂያ

በ2014 ዓም. 12ኛ ክፍል የላቀ ዉጤት አምጥታችሁ የዉጪ ሀገር የትምህርት እድል/Scholarship / እድል ለተሰጣችሁ 273 ተማሪዎች

በ2014 ዓም. 12ኛ ክፍል የላቀ ዉጤት አምጥታችሁ የዉጪ ሀገር የትምህርት እድል/Scholarship / እድል የተሰጣችሁ 273 ተማሪዎች የዉጪ ሀገር ትምህርቱ የሚጀመረዉ ከመስከረም/2016ዓም. ጀምሮ በመሆኑ ቀደም ሲል ወደተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርስቲዎች እንድትገቡ እናሳስባለን፡፡

ለዉጪ ሀገር ትምህርታችሁ የሚያግዝ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመነጋገር የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ማስታወሻ፤- በዚህ ጉዳይ በተናጠል ወደትምህርት ሚኒስቴር የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር!