Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ቤቶች ለስርዓተ ፆታና አካቶ ትምህርት ምላሽ ሰጪና ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ ተገ | ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ቤቶች ለስርዓተ ፆታና አካቶ ትምህርት ምላሽ ሰጪና ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
-------------------------------------------------
መጋቢት 14/2015ዓ.ም. (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር በስርዓተ ፆታና አካቶ ትምህርት ላይ ትኩረት ያደረገ የአሰልጣኞች ስልጠና ከክልልና መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ለተውጣጡ መምህራንና የክልል ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡

የስልጠናው ዓላማም የስርዓተ ፆታና አካቶ ትምህርት ተሳትፎ ውጤታማነትን ለማሻሻል እና ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ክህሎት ለመገንባት መሆኑ ተገልጿል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ ስልጠናው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስርዓተ ፆታ ተኮር ጉዳዮችን መሰረት ያደረጉ አካታች ውጤታማ ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

ሁሉም ልጆች የመማር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል ትምህርት ቤቶችን አካታችና ምቹ የትምህርት አካባቢ ማድረግ ይገባልም ብለዋል፡፡

በተለይም በትምህርት ዘርፉ የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማስፈንና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ተሳትፎን ለማሳደግና ውጤታማነትን የሚያረጋግጥ አካታች ትምህርት መስጠትና የሴት ልጆችን ውጤታማትነት ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገብልም ተብሏል፡፡

ሙሉ ዜናውን

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid07niRKUxkegNSwc3YAC6aRGAraHNWfKdD7hp76oXTRPHQK46g6WvE89zU96J8Kodml&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz