Get Mystery Box with random crypto!

መርጌታ ጥላሁን

የቴሌግራም ቻናል አርማ timhrtministers — መርጌታ ጥላሁን
የቴሌግራም ቻናል አርማ timhrtministers — መርጌታ ጥላሁን
የሰርጥ አድራሻ: @timhrtministers
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.21K
የሰርጥ መግለጫ

ለተማሪዎች በቀላሉ የትምህርት መረጃዎችን, መፅሀፎችን, ኖቶችን, ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ሁሉንም በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው::
ለማንኛውም መልዕክት
@Nextmis
@Nextmis

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-13 20:59:13
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ ን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሰራጭቷል።

በ2015 የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚሆነው መመሪያው፤ የከፍተኛ ትምህርት የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ወሳኝ ነው ተብሏል።

መመሪያ ቁጥር 919/2014 ሆኖ በፍትህ ሚኒስቴር የጸደቀውን መመሪያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ መሰራጨቱ ታውቋል።

አምስት ክፍሎች እና 27 አንቀጾች ያሉት አዲሱ መመሪያ፤ ከነሐሴ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ የጸና እንደሆነ ተደንግጓል።

በመመሪያው ላይ የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በማንኛውም ሁኔታ የጣሰ፣ እንዲጣስ ያደረገ በማንኛውም ደረጃ ላይ ያለ አስፈጻሚና ፈጻሚ አካል ተጠያቂ እንደሚሆን በመመሪያው ተመላክቷል።
https://t.me/Timhrtministers
2.3K viewsedited  17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 17:33:15 ማንኛውም የግል ትምህርት ቤት መፅሃፍም ሆነ ደብተር መሸጥ እንደማይችል ማሳሰቢያ ተሰጠ

አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ፤ መጽሐፍም ሆነ ደብተር ለመሸጥ አይደለም ሲል የ #አዲስአበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከመመሪያ ውጪ ያልተገባ ክፍያ አስከፍለው በተገኙ ተቋማት ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።።

በመመሪያ አተገባበሩ ላይ የተለያዩ ጥቆማዎች እየደረሱ እንደሚገኝም ኃላፊዋ አክለዋል። በመመሪያ አተገባበሩ ላይ ከመጡት ጥቆማዎች ውስጥ አንዳንድ ተቋማት የምዝገባ ክፍያ መጨመር፣ በዓይነት መቀበል ለአብነት እሽግ ወረቀት እና የመፀዳጃ ቤት የንፅህና እቃዎችን የሚጠይቁ እንዳሉበት ገልፀዋል።

በተጨማሪም ባልተፈቀደ ክፍያ ጭማሪ እያደረጉ ያሉ የትምህር ተቋማት እንደሚገኙ ጥቆማ ደርሶናል ወርደን እናስተካከልን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ ክፍያ ውጪ በየትኛውም መልኩ ክፍያ ማስከፈል አይቻሉም፤ አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ መጽሐፍም ሆነ ደብተር ለመሸጥ አይደለም ብለዋል።ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ በሚገኝ ተቋም ላይ ርምጃ ይወሰድበታል፤ የሰበሰበውን ገንዘብም ሆነ ማንኛውንም አይነት ቁሳቁስ እንዲመልስ ይደረጋል ሲሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
https://t.me/Timhrtministers
https://t.me/Timhrtministers
2.9K viewsedited  14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 14:00:33
#Update: የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀው ነበር።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ብሏል።
https://t.me/Timhrtministers
3.2K viewsedited  11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ