Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እ | መርጌታ ጥላሁን

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች የ2015 ዓ.ም የትምህርት ካላንደር ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ታሳቢ ያደረገ መሆን እንደሚገባው ተገልጿል።

ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ እና ለፈተና ማቆያ ቦታ እና የምግብ አቅርቦት ዝግጅት እንዲደረግም ትእዛዝ ተላልፏል።

ከፈተና ደህንነት እና አቅርቦት ጋር በተያያዘ የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሚመራ ዋና ግብረ ኃይል እንዲሁም በካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ ኃይል እንዲደራጅም ሚኒስቴሩ መመሪያ አስተላልፏል፡፡

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወሳል።

https://t.me/Timhrtministers