Get Mystery Box with random crypto!

#መውጫ_ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ዓመት 2015 ትምህርት ዘመን የሚጀምረውን የከፍተኛ | መርጌታ ጥላሁን

#መውጫ_ፈተና

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ዓመት 2015 ትምህርት ዘመን የሚጀምረውን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአፈፃፀም መመሪያን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማሰራጩት ይታወቃል።

ለመሆኑ መመሪያው ምን ይላል ?

- የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያ ዲግሪ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ይመለከታል።

- መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚከወኑ የማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው።

- የመውጫ ፈተናውን ወስዶ 50 በመቶ ውጤት ማምጣት ያልቻለ ተማሪ መመረቅም ሆነ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ የዲግሪ ሰርተፊኬት ማግኘት አይችልም።

- በመውጫ ፈተና 50 በመቶ ማምጣት ያልቻለ ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ በአግባቡ አጥንቶ ፈተናውን 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥቶ ማለፍ እንዲችል ለሁለት ተጨማሪ ጊዜ የመፈተን እድል ይሰጠዋል። ተፈታኙ እድሉን መጠቀም ያለበት የመጀመሪያውን ፈተና ከወሰደ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው።

- አንድ ተማሪ ለምርቃት ብቁ የሚሆነው የመውጫ ፈተናውን ካለፈ ብቻ ሲሆን 3 ጊዜ ተፈትኖ የማለፊያ ነጥብ ያላገኘ ተፈታኝ ከብሄራዊ የብቃት ማዕቀፍ ተገቢው ማስረጃ ይሰጠዋል።

- የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና እንደየትምህርት ፕሮግራሙ ባህሪ በዓመት ሁለቴ እና ከዛም በላይ ሊሰጥ ይችላል።

- የመውጫ ፈተና የሞያ ማህበራት ተጠናክረው የሞያ ፍቃድ ፈተና መስጠት እስከሚጀምሩ በትምህርት ሚኒስቴር ወይም ውክልና በሚሰጠው ተቋም ይዘጋጃል።

መውጫ ፈተና ላይ ሚካተቱ ኮርሶችን በተመለከተ በመጪው ጊዜ በየትምህርት መስኩ በሚዘጋጁ የማስፈፀሚያ ዝርዝር መመሪያዎች ይለያል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ካሰራጨመው ዘገባ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።