Get Mystery Box with random crypto!

ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 አመታት በፊት ከአሻንቲ የተዘረፉ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለጋና | TIKVAH-MAGAZINE

ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 አመታት በፊት ከአሻንቲ የተዘረፉ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለጋና በውሰት መለሰች

ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 ዓመታት በፊት በብሪቲሽ እና ታዋቂ በነበሩት የአሻንቲ ህዝቦች መካከል በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ከአሻንቲ ንጉስ ፍርድ ቤት ተዘርፈው የተወሰዱ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለስድስት አመታት ውል በውሰት ለጋና መስጠቷ ተገለፀ።

ቅርሶቹ ሊመለሱ የቻሉት የወቅቱን የአሳንቲ ንጉስ የሆኑት "ኦቱምፉኦ ኦሴይ ቱቱ 2ኛ" የብር ኢዮቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚቀጥለው ወር በአሻንቲ ክልል ርዕሰ መዲና በሚገኘው በማኒሺያ ቤተ መንግስት ሙዚየም ለእይታ እንዲቀርቡ ታልሞ መሆኑ ተጠቁሟል።

ዩናይትድ ኪንግደም እነዚህ ቅርሶች የመለሰችው የአውሮፓና የአሜሪካ ሙዚየሞችና ተቋማት እንደ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቤልጂየም ባሉ ኃያላን አገሮች በቅኝ ግዛት ዘመን የዘርፏቸውን የአፍሪካ ቅርሶች እንዲመለሱ ግፊት እየተደረገባቸው ባለበት ወቅት መሆኑም ነው የተገለፀው።

@tikvahethmagazine