Get Mystery Box with random crypto!

የመንግስትን እና የሀይማኖት ተቋማትን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ መንግሥትና | TIKVAH-MAGAZINE

የመንግስትን እና የሀይማኖት ተቋማትን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

መንግሥትና ሃይማኖት አንዱ በአንዳቸው ተግባርና እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያለው ድንጋጌ ሃይማኖትና መንግሥት አይደራረሱም ማለት እንዳልሆነ ሲገለጽ በጋራ የሚሠሩባቸው ጉዳዮች መኖራቸውንና ሆኖም በሕገ መንግሥቱ ያለው ድንጋጌ ጥቅል መርሆዎችን የያዘ በመሆኑ፣ ይህን ለማብራራት ሕግ በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉባቸው ሦስት ጥናቶች ተካሂደው ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከተወሰኑ ቤተ እምነቶች ጋር ውይይት የተጀመረ መሆኑን በሰላም ሚኒስቴር የሃይማኖት ጉዳዮች ዴስክ ተጠባባቂ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀለፎም ዓባይነህ፣ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

@tikvahethmagazine