Get Mystery Box with random crypto!

የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ እንዲፀድቅ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ ተነገረ በ | TIKVAH-MAGAZINE

የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ እንዲፀድቅ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ ተነገረ

በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቅቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ተብሏል።

መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሲገለፅ ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine