Get Mystery Box with random crypto!

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳት 75 በመቶ መድረሱ ተገለፀ የመንበረ ጸባኦት ቅድ | TIKVAH-MAGAZINE

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳት 75 በመቶ መድረሱ ተገለፀ

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳት በ172 ሚሊየን ብር እየተከናወነ ሲሆን የጥገና ሥራው 75 በመቶ መድረሱ ተገለፀ።

እድሳቱ በውሉ መሰረት መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም መጠናቀቅ ቢጋባውም በገቢ ማነስ እና ህንፃውን ለማጠናቀቅ የሚረዱ ግብአቶች ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር መሆኑ ተገልጿል።

የካቴድራሉ እድሳት ለማጠናቀቅ 85 ሚሊየን ብር መሰብሰብ እንደሚጠይቅ የተገለፀ ሲሆን የካቴድራሉን እድሳት ከፍጻሜ ለማድረስ  አስተዋጽኦ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

@TikvahethMagazine