Get Mystery Box with random crypto!

ዩናይትድ ኪንግደም የህጻናት ደፋሪዎችን የወላጅነት መብት የሚነጥቅ ህግ ልታወጣ ነው ዩናይትድ ኪን | TIKVAH-MAGAZINE

ዩናይትድ ኪንግደም የህጻናት ደፋሪዎችን የወላጅነት መብት የሚነጥቅ ህግ ልታወጣ ነው

ዩናይትድ ኪንግደም በከባድ ወሲባዊ ጥቃቶች የተከሰሱ ህጻናት ደፋሪዎች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን መብት የሚነጥቅ ህግ ልታወጣ መሆኑ ተሰምቷል።

አዲስ ለሆነው ለዚህ ህግ መነሻ የሆነው አንዲት እናት ህጻናትን ደፋሪ ነው የተባለው የቀድሞ ባለቤቷ ከልጃቸው ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ 30 ሺህ ፓውንድ ለህጋዊ ክፍያ ማውጣታቸውን ተከትሎ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

በዚህም በወሲባዊ ጥቃቶች ጥፋተኛ የሆኑ በህጻናት ላይ ወሲባዊ ዝንባሌ ያላቸው ግለሰቦች (ፒዶፋይልስ) የወላጅነት መብታቸውን ወዲያውኑ የሚገፈፍ ይሆናል ተብሏል። የፍ/ቤቶች፣ የማረሚያ ቤቶች፣ የአመክሮና የህገመንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለው ሎርድ ቻንስለር በህጉ ላይ መስማማታቸውም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine