Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ አሳሳቢነቱ በጎላው የጋዜጠኞች እሥር እና ሌሎች ጉዳዮች ከጋዜጠኞች | TIKVAH-MAGAZINE

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ አሳሳቢነቱ በጎላው የጋዜጠኞች እሥር እና ሌሎች ጉዳዮች ከጋዜጠኞች ጋር እንዲወያዩ ጥያቄ ቀረበ

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ አሳሳቢነቱ በጎላው የጋዜጠኞች እሥር እና እንግልት፣ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ያሉባቸው ችግሮች ላይ ከመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እና ጋዜጠኞች ጋር ውይይት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠየቀ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ይህንን የጠየቀው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ያደረጉትን ተከታታይ ውይይት አስመልክቶ ሲሆን የውይይት ጥያቄውን ከሦስት ሳምንት በፊት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ማስገባቱን እና ምላሽም እየተጠባበቀ መሆኑን ዶይቸ ቬለ ዘግቧል።

በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገውና  ከ80 በላይ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን ፣ የሙያ ማሕበራትን እና የበይነ መረብ እንዲሁም የማኅበረሰብ መገናኛ ብዙኃንን ያቀፈው ምክር ቤቱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተከታታይ ውይይት ሲያደርጉ ነገር ግን ላለፉት 6 ዓመታት ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ከጋዜጠኞች ጋር በዘርፉ ላይ ስላሉ ችግሮችን ውይይት #አለመደረጉን አስታውሷል።

@TikvahethMagazine