Get Mystery Box with random crypto!

የውጭ ባለሀብቶች በጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባ | TIKVAH-MAGAZINE

የውጭ ባለሀብቶች በጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ

ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ መደረጉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የውጭ ባለሀብቶች በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላክ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟሉ የውጭ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢ ንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት ይችላሉ ተብሏል።

የጅምላ ንግድን በተመለከተ ከማዳበሪያ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይቻላል ሲባል በተጨማሪም የውጭ ባለሀብቶች ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያሟሉ ለአገር ውስጥ ባለሃብት በተከለሉ ሁሉም የችርቻሮ ንግድ ስራዎች መሳተፍ እንዲችሉ መፈቀዱንም ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@TikvahethMagazine