Get Mystery Box with random crypto!

በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን ውድድር የተፈጠረው ምንድን ነው? በቤጂንግ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ው | TIKVAH-MAGAZINE

በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን ውድድር የተፈጠረው ምንድን ነው?

በቤጂንግ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች አንድ ቻይናዊ አትሌት ተባብረው እንዲያሸንፍ አድርገዋል፤ የውድድር ህግ ጥሰዋል በሚል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

በውድድሩ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊ አትሌት ደጀኔ ኃይሉ ጨምሮ ሁለት ኬኒያዊያን አትሌቶች ሂ ጃይ (He Jie) የተሰኘውን ቻይናዊ አትሌት በውድድሩ ማገባደጃ ላይ በእጃቸው እንዲፈጥን በመጠቆም እንዲሁም ፍጥነታቸውን በመቀነስ አትሌቱ አሸናፊ እንዲሆን አድርገዋል በሚል ነው ምርመራው የተከፈተው።

ይህ ቪዲዮ በቻይና በሚገኙ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተለቀቀ በኋላ በርካቶች ድርጊቱን የተቃወሙት ሲሆን የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችንም ትኩረት ስቧል።

ከኬኒያውያን አትሌቶች አንዱ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ እንደገለጸው ሦስታችንም በውድድሩ የተሳተፍነው ቻይናዊውን አትሌት ለማሯሯጥ (pacemaker) ነው ሲል ገልጿል

አትሌቱ እንደገለጸው ቻይናዊው አትሌት የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውድድርን ሪከርድ የሆነውን 1:02:33 እንዲሰብር ለማገዝ ብንገባም ማሳካት አልተቻለም ብሏል። ቻይናዊው አትሌት ውድድሩን ማጠናቀቅ የቻለው በ1:03:44 ነው።

የቤጂንግ ስፖርት ቢሮ ቃል አቀባይ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት ጉዳዩን እየመረመሩ መሆኑን ገልጸው “ውጤቱን እንደተገኘ ለህዝብ እናሳውቃለን” ብለዋል።

@TikvahethMagazine