Get Mystery Box with random crypto!

#Update: በኢትዮጵያ ለተከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ አስቸኳይ 1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ የማሰባሰብ ሥ | TIKVAH-MAGAZINE

#Update: በኢትዮጵያ ለተከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ አስቸኳይ 1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ የማሰባሰብ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

በስዊትዘርላንድ ጄኔቫ ዛሬ ሚያዚያ 8/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለተከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ የ1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ  የማሰባሰብ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ። በስርዓትቱም ዩናይትድ ኪንግደም 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደምታደርግ አስታውቃለች።

የገንዘብ ድጋፉን ሥነ ሥርዓት ያዘጋጁት የኢትዮጵያ፣ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተባባሪ አካላት ለቀረበው የገንዘብ ድጋፍ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ የሚጠብቁ መሆኑን ገልፀዋል።

በሀገቱ በድርቅ፣ ጎርፍ እና ግጭት ሚሊዮኖችን ከቀያቸው ያፈናቀለ ሲሆን፣ በመጪዎቹ ከሐምሌ 2016 እስከ መስከረም 2017 መካከል የምግብ እጥረት የሚገጥማቸው ሰዎች ቁጥር 10.8 ሚሊዮን እንደሚደርስ ተገምቷል።

@TikvahethMagazine