ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ የሚላኩ የአበባ ምርቶች ያለ ቀረጥ ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ ፈቀደች
ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ እና ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ ርካሽና ተመጣጣኝ ለማድረግ በማለም ከቀጠናው ሀገራት የሚላኩ አበቦች ትቆርጥ የነበረውን የቀረጥ ክፍያ ለ2 አመት አነሳች።
ከዚህ በፊት የአበባ ምርቶች ወደ ብሪታኒያ ሲገቡ 8 በመቶ ቀረጥ መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የቀረጥ ክፍያው የሚነሳ መሆኑን ብሪታኒያ ባወጣችው መግልጫ አስታውቃለች።
ይህ የ 8 በመቶ የቀረጥ ክፍያ ከመላው ዓለም የአበባ ምርቶችም ወደ ሀገሪቱ የሚልኩ ሀገራትን ተጠቃሚ ያደርጋል ሲባል ነገር ግን ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ላሉ ዋና የአበባ አምራች ሀገራት ትልቅ አጋጣሚ ይፈጥራል ተብሏል።
ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት 23 በመቶ የሚሆነውን የአበባ ምርት ወደ ውጪ የምትልክ ሲሆን በአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ የአበባ አምራች ነች። በ 2023 ወደ ብሪታኒያ የላከችው የአበባ ንግድ ዋጋ 12.6 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሆነም የብሪታኒያ መንግስት አሳውቋል።
@TikvahethMagazine