Get Mystery Box with random crypto!

' ያለቡና መኖር አንችልም ' የኢትዮጵያ ቡና አምራች አርሶ አደሮች የአውሮፓ ህብረት በ 2025 | TIKVAH-MAGAZINE

" ያለቡና መኖር አንችልም " የኢትዮጵያ ቡና አምራች አርሶ አደሮች

የአውሮፓ ህብረት በ 2025 ተግባራዊ ሊያደይርገው ያቀደው የፀረ ደን ጭፍጨፋ ደንብ (EUDR)  የኢትዮጵያ የአነስተኛ የቡና ምርት አምራች ገበሬዎች ህይወት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ቡና አምራቾች ገለፁ።

የአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የኑ ምርቶች #ብቻ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት እንዲገቡ በሚፈቅደው የ EUDR ደምብ ምክንያት ከአውሮፓ ሀገራት የሚመጣው የቡና አቅርቦት ጥያቄ እየቀነሰ መሆኑን የከፋና ሲዳማ ቡና አምራቾች ለ ዘጋርዲን ተናግረዋል።

እንደ ህጉ መሰረት በአውሮፓ ህብረት ገበያ ላይ መቅረብ የሚችሉት ምርቶች ህጋዊ የሆኑ፣ ከደን መጨፍጨፍና መራቆት ጋር ያልተገናኙ ምርቶች ብቻ ናቸው። ከዚህ ጋር ተያይዞ " መስፈርቶቹን ማሟላት ትላልቅ ቴክኖሎጂ እና ብዙ የሰው ሀይል ይፈልጋል። እኛ ደግሞ ይህንን የለንም " ሲሉ የከፋ ቡና አምራች ህብረት ሀላፊ ገልፀዋል።

ከአውሮፓ ህብረት 27 አባል ሀገራት 20 ያህሉ የፀረ-ደን መጨፍጨፍ ህጉ እንዲዘገይ እና አነስተኛ የደን መጨፍጨፍ አደጋ አለባቸው ተብለው በሚታሰቡ አገሮች የሚገኙ አምራቾችን ታሳቢ በማድረግ ከህጉ ነፃ እንዲያደረጉ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ህብረቱን ጠይቀዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በአይቮሪ ኮስት የሚገኙ የካካዎ አምራቾች እንዲሁም የፓልም ዘይት አምራቿ ኢንዶኔዥያ የህጉ ተፈፃሚነት እንዲዘገይ ይፈልጋሉ ተብሏል።

ይህንን አስመልክቶ ከቀናት በፊት የአውሮፓ የአካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ቨርጂኒጁስ ሲንኬቪሲየስ ህጉ ከ2025 መጀመሪያ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ የአውሮፓ ህብረት ህጉ ተግባራዊ የሚደረግበት ጊዜ እንደማይራዘም ለሮይተርስ ተናግረዋል።

@TikvahethMagazine