Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉ ከ 700 በላይ እግረኞች በገንዘብና ማህበራዊ አገ | TIKVAH-MAGAZINE

በመዲናዋ ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉ ከ 700 በላይ እግረኞች በገንዘብና ማህበራዊ አገልግሎት ተቀጡ

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመት ባለስልጣን በከተማዋ ከመጋቢት 13 ጀምሮ ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉና ደንብ የተላለፉ እግረኞችን እየቀጣ ሲሆን እስካሁን 777 እግረኞች የገንዘብ እና የማህበራዊ አገልግሎት የመስጠት ቅጣት እንደተቀጡ ኢፕድ ዘግቧል።

በመቆጣጠሪያ ደንብ መሰረት እግረኞች ጥፋት ሲያጠፉ የሚጣለው ቅጣት ምን ይመስላል ?

ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርግ መንገድ ያቋረጠ፤ ለተሸከርካሪ በተፈቀደ መንገድ ላይ ያለ በቂ ምክንያት የቆመ ወይም የተጓዘ ብር 40፤

እግረኛ መንገድ በሌለበት ቀኝ ጠርዙን ይዞ የተጓዘ፤ ለእግረኛ መንገድ ተብሎ ከተከለለ ውጭ የተጓዘ ብር 40 ይቀጣል።

ለእግረኛ መንገድ ላይ ንግድ ያከናወነ ወይም ቁሳቁስ ያስቀመጠና በእግረኞች እንቅስቃሴ እንቅፋት የሆነ ብር 80፤

በብረትም ሆነ በግንብ ተለይተው የታጠሩ መንገዶችን ዘሎ ያቋረጠ፤ ጆሮ ማዳመጫ የተለያዩ ድምጾችን እያዳመጠ መንገድ ያቋረጠ ብር 80፤

"ለእግረኛ ክልክል ነው" የሚል ምልከት ባለበት መንገድ ወይም እግረኛ እንዳያቋርጥ በተከለከለበት የማሳለጫ ወይም ቀለበት መንገድ ያቋረጠ ብር 80 ይቀጣል።

እነዚህን ጥፋቶች አንዱን ፈጽሞ ክፍያ መፈጸም ያልቻለ ወይም ያልፈለገ ማንኛውም እግረኛ ተመጣጣኝ የሆነ የማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል።

በማስፈጸሚያ መመርያው መሰረት የ40 ብር ቅጣት የ30 ደቂቃ ማህበራዊ አገልግሎት ፤ ባለ 80 ብር ቅጣት የ1 ሰዓት ማህበራዊ አገልግሎት ቅጣት የሚያስጥል መሆኑ ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine