Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቆማ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ህክምና ክፍል እ | TIKVAH-MAGAZINE

#ጥቆማ

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ህክምና ክፍል እና ኤች.ሲ.ፒ ኪዩር ብላይንድስ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ከሚያዝያ 7 እስከ ሚያዝያ 11 ፥ 2016 ዓ/ም ድረስ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ለ 450 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህሙማን ነፃ ህክምና እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ስለሆነም የህሙማን ቅድመ ልየታ ስራ ከፊታችን ሐሙስ ሚያዝያ 3 ፥ እስከ 4 - 2016 ዓ.ም በሆስፒታሉ ውስጥ የሚከናወን ሲሆን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህመም ያለባችሁ ታካሚዎች በተጠቀሱት የቅድመ ልየታ እና የህክምና ቀናት በሆስፒታሉ ውስጥ በመገኘት የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥቆማ ቀርቧል።

አድራሻው አዲስአበባ ፤ ጉለሌ ክ/ከተማ ፤ ወረዳ 1፣ ከሽሮሜዳ ወደ ቁስቋም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሆን ታካሚዎች ለበለጠ መረጃ በሆስፒታሉ ነፃ የስልክ መስመር 998 ላይ መደወል ይችላሉ ተብሏል።

@TikvahethMagazine