የአፍሪካ ኅብረት ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ የዘር ማጥፋትና የጅምላ ጭፍጨፋን ለመከላከል ልዩ መልዕክተኛ ሾመ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሌሎች ጅምላ ጭፍጨፋዎችን ለመከላከል ሴኔጋላዊውን አዳማ ዲዬንግ የመጀመሪያ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ አድርገው ሾመዋል። ልዩ መልዕክተኛው የተሾሙት በአፍሪካ አህጉር የጥላቻ እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ለመዋጋት የተያዘውን የህብረቱን አጀንዳ ለማስፈፀም ሲሆን ዲዬንግ በቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን የጅምላ ጭፍጨፋ መከላከል ልዩ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል ተብሏል። @TikvahethMagazine 25.3K views13:13