Get Mystery Box with random crypto!

በቀጣይ ዓመት ብሔራዊ መታወቂያ የሌላቸው ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት አያገኙም ተባ | TIKVAH-MAGAZINE

በቀጣይ ዓመት ብሔራዊ መታወቂያ የሌላቸው ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት አያገኙም ተባለ

በሚቀጥለው ዓመት የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት ለማግኘት ብሔራዊ መታወቂያ ያስፈልጋል በማለት በቀጣይ ዓመት ብሔራዊ መታወቂያ የሌላቸው ነጋዴዎች አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ደንበኞች በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው በኦንላይን አገልግሎት እያገኙ ነው ሲባል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ከሌሎች ተቋማት ጋር የሚያገናኘው በመሆኑ ከተቋማቱ ጋር ሲስተም የማናበብ ስራ በፋይዳ መለያ የሚሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።

ስለዚህ የንግዱ ማህበረሰብ ከ2017 በፊት ብሔራዊ መታወቂያ በማውጣት ራሱን ለነገሮች ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የላይሰንሲንግ እና ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጅራታ ነመራ ተናግረዋል።

Credit : EPA

@TikvahethMagazine