Get Mystery Box with random crypto!

#Update: 70 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከሳውዲ አረቢ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ሁኔታዎች | TIKVAH-MAGAZINE

#Update: 70 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከሳውዲ አረቢ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ሁኔታዎችን የሚያመቻች ልዑክ ወደ ሳውዲ ሊያቀና ነው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 70ሺህ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ሁኔታዎችን የሚያመቻች በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግሥት ልዑክ በቀጣይ ቀናት ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንደሚያቀና ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ክቡር አቶ ነብዩ ተድላ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ልዑኩ በሳዑዲ በሚኖረው ቆይታ አስፈላጊውን ዝግጅት ካጠናቀቀ በኋላ በፍጥነት ዜጎችን የመመለስ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጸዋል።

@TikvahethMagazine