Get Mystery Box with random crypto!

ጁምዓና ከተራን ጨምሮ አራት ቀናት ሥራ ዝግ ሆኖ እንዲከበሩ ጥያቄ ቀረበ ጁምዓ፣ ከተራና ቃና ዘገ | TIKVAH-MAGAZINE

ጁምዓና ከተራን ጨምሮ አራት ቀናት ሥራ ዝግ ሆኖ እንዲከበሩ ጥያቄ ቀረበ

ጁምዓ፣ ከተራና ቃና ዘገሊላ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ እንዲሁም የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በዓላት ሥራ ዝግ ሆነው እንዲከበሩ በፓርላማ ጥያቄ መቅረቡን ሪፖርተር አስነብቧል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጤና፣ የሕዝብ በዓላትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የሕዝብ ውይይት የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ምሁራንና ሌሎች ተቋማት ተሳትፈዋል።

ተሳታፊዎቹ ምን ጥያቄ አቀረቡ?

- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በመወከል የተገኙት ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ በእስልምና አንድ ሰው 3 ተከታታይ ጁምዓ ካልተገኘ በመናፍቅነት የሚያስፈርጅ ከባድ ጉዳይ በመሆኑ፣ ዓርብ (ጁምዓ) ቀን ሥራ ዝግ እንዲሆን፣ ወይም ደግሞ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ከአምስት ሰዓት ተኩል እስከ ሰባት ሰዓት ተኩል በአዋጁ መካተት አለበት ብለዋል።

- ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያሪክ የሕግ መምርያ ኃላፊ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት፣ እየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ባህረ ዮርዳኖስ ሄዶ መጠመቁን የሚያሳየው የቃል ኪዳኑን ታቦት በመያዝ ጥር 10 ቀን የሚከበረው ከተራና ከጥምቀት በኋላ ጥር 12 ቀን የሚከበረው ቃና ዘገሊላ ክብረ በዓላት ከሥራ ዝግ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

- በተጨማሪም የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ታስቦ ከመዋል ይልቅ ከሥራ ዝግ ሆኖ መከበር ይገባዋል ያሉት ደግሞ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር) ናቸው፡፡

የተሰጡ አስተያየቶች ረቂቅ አዋጁን ለማጎልበት እንደሚያግዝ ሲገለፅ፣ አዋጁ ኢትዮጵያውያንን እንዲመስል ዘላቂነት ያለው ውይይት እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine