Get Mystery Box with random crypto!

በወልቂጤ ተጣምረውና ተዋህደው የተወለዱ መንትዮች በተሳካ ቀዶ ህክምና እንዲለያዩ ተደረገ የወልቂጤ | TIKVAH-MAGAZINE

በወልቂጤ ተጣምረውና ተዋህደው የተወለዱ መንትዮች በተሳካ ቀዶ ህክምና እንዲለያዩ ተደረገ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
የተዋሃዱ ወይም የተጣመሩ መንትዮችን በቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ እንዲለያዩ ማድረጉን አስታውቋል።

የቀዶ ህክምናው የተሰራው በሆስፒታሉ የህፃናት ስፔሻሊስት ሃኪም በሆኑት ዶ/ር ሙሉአለም አማረ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የተዋሃዱ ወይም የተጣመሩ መንትዮች ክስተት እርግጠኛ ያልሆነ ፅንስ መከሰትን የሚጠቁም እንደሆነና ባለሙያው ሞኖዚጎቲክ መንትዮች የሚፈጠሩት ከአንድ ቀደምት ፅንስ ክፍፍል እና መለያየት እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህ መሰረት በተደረገው የቀዶ ህክምና አገልግሎት አንደኛው ህጻን በህይወት የተወለደ ሲሆን ህፃኑ በተወለደ በአምስተኛ ቀኑ ከራሱ ጋር ተጣብቆ የተወለደውንና በህይወት ከሌለው መንትያ ጋር በመለየት በህይወት የተረፈው ህጻን በሰላም ወደ ቤቱ መመለሱን ባለሙያው ገልጸዋል።

ይህን መሰል ክስተት የስርጭት መጠኑ ቀደም ሲል ከ50,000 እስከ 100,000 ከሚወለዱ ሕፃናት መካከል በአንዱ የሚከሰት ሊሆን እንደሚችል ዶ/ር ሙሉአለም አማረ አብራርተዋል።

@TikvahethMagazine