በአፍሪካ ለነዳጅ እና ጋዝ ፕሮጀክቶች ብድር የሚያቀርበው የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ በዚህ አመት ስራ ይጀምራል ተባለ
አፍሪካ የነዳጅ እና ጋዝ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ የመደገፍ ስራ ይሰራል የተባለው የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ በዚህ አመት በ5 ቢሊዮን ዶላር መነሻ ካፒታል በ2024 ስራ ሊጀምር መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባንኩ የተቋቋመው በአፍሬክሲም ባንክ እና በአፍሪካ ፔትሮሊየም አምራቾች ድርጅት (ኤፒፒኦ) ሲሆን ዋናዎቹ ባንኮች በአየር ንብረት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የነዳጅ ፕሮጀክቶችን በመተው ኢንቨስትመንቶቻቸውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲቀይሩ ከአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ከፍተኛ ጫና እያጋጠማቸው በመሆኑ ዘርፉ የፋይናንስ እጥረት ችግር ውስጥ ገብቷል ተብሏል።
ይህ ባንክ በአፍሪካ ኢነርጂ ዘርፍ ያለውን ይህንን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ ሚና ይኖረዋል ሲባል ካፒታሉን ለማሰባሰብ እያንዳንዱ የአፍሪካ አባል ሀገር ቢያንስ 83 ሚሊዮን ዶላር መለገስ እንደሚጠበቅበትና ቀሪው ገንዘብ ከመካከለኛው ምስራቅ አማራጭ የፋይናንስ ምንጮች ይሰበሰባል ተብሏል።
@TikvahethMagazine