Get Mystery Box with random crypto!

አካል ጉዳተኞችን የተመለከተ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑ ተሰማ አካል ጉዳተኞች መብታቸው እ | TIKVAH-MAGAZINE

አካል ጉዳተኞችን የተመለከተ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑ ተሰማ

አካል ጉዳተኞች መብታቸው እንዲጠበቅ ለመብታቸው መጠበቅም ምላሽ የሚሰጥ ተፈጻሚነቱን የሚከታተል ባለቤት ያለው አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊወጣ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞችን መብት ምላሽ የሚሰጥ ጥቅል አዋጅ የላትም የተባለ ሲሆን ያን ለማድረግ የአካል ጉዳተኞች ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ወደ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩ ተገልጿል።

ይህ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ ፥ ያሉትን ህጎች ተከታትሎ የሚያስፈፅም፣ ካልተፈፀሙም ተጠያቂ የሚሆን ተቋም እንዲኖር ለማስቻል ፣ የህግ ክፍቶችም እንዲስተካከሉ ያደርጋል ተብሏል። አዋጁ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተልኮ አስፈላጊ አስተያየት ከተሰጡበት በኋላ ወደ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩ ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine