Get Mystery Box with random crypto!

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣዮቹ አስር ቀናት አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ይጀምራል ተባለ በቀጣዮቹ አ | TIKVAH-MAGAZINE

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣዮቹ አስር ቀናት አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ይጀምራል ተባለ

በቀጣዮቹ አስር ቀናት ውስጥ በተመረጡ ክልሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መግለፁን ኢፕድ ዘግቧል።

አሁን ላይ ኮሚሽኑ በ10 ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ አጠናቅቋል። የአጀንዳ ማሰባሰቡ ሥራ በአዲስ አበባ፣ በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በሲዳማ፣ በሐረር እንዲሁም በድሬዳዋ እንደሚጀመር ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine