Get Mystery Box with random crypto!

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ባስጀመረው የንባብ ዘመቻ በበርካታ ሰዎች የተጠቆሙት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው | TIKVAH-MAGAZINE

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ባስጀመረው የንባብ ዘመቻ በበርካታ ሰዎች የተጠቆሙት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው ?

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬድዮ ከየካቲት 17 እስከ ግንቦት 27 /2016 ዓ.ም ለ100 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የንባብ ዘመቻ ማስጀመሩ ይታወሳል። እስካሁን የመጻሕፍት ምርጫቸውን በማሳወቅ ጥቆማ የሰጡ ሰዎች ሰላሳን ተሻግረዋል።

የመጻሕፍት ጥቆማቸውን ይፋ ባደረጉት የጀመሪያዎቹ 30 ሰዎች ዘንድ የትኞቹ መጻሕፍት በተደጋጋሚ ተመረጡ ?

1) የሀዲስ አለማየሁ "ፍቅር እስከ መቃብር" በ 9 ሰዎች የንባብ ጥቆማ ዝርዝር ውስጥ ተካትቷል።

2) የሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን " እሳት ወይ አበባ "  በ5 ሰዎች የንባብ የንባብ ዝርዝር ውስጥ መግባት ችሏል።

3) የሀዲስ አለማየሁ " ትዝታ " በ 3 ሰዎች፤

4) የቀዳማዊ አፄ ሀይለስላሴ " ሕይወቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ " በ 3 ሰዎች፤

5) የበዓሉ ግርማ " ኦሮማይ " በተመሳሳይ በ3 ሰዎች የንባብ ምርጫ ውስጥ መካተት ችሏዋል።

የሚከተሉት 6 መጻሕፍት ደግሞ እያንዳንዳቸው በ 2 ሰዎች የንባብ ጥቆማ ዝርዝር ውስጥ መካተት ችለዋል።

1)  የፊዮዶር ዶስቶቭስኪ " ወንጀል እና ቅጣት "

2) የእጓለ ገ/ዮሐንስ " የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ"

3) የተመስገን ገብሬ " ሕይወቴ "

4)  የፋሲካ ሲደልል " የሻምላው ትውልድ "

5) የመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ " የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ "

6) የዳኛቸው ወርቁ " አደፍርስ "

@TikvahethMagazine