Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ አሳሳቢ የጤና ችግሮችን ለመፍታት የሚውል 1.8 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ ጃ | TIKVAH-MAGAZINE

በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ አሳሳቢ የጤና ችግሮችን ለመፍታት የሚውል 1.8 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ ጃፓን አሳወቀች

በሰሜን ኢትዮጵያ የጤናና ስነ ምግብ አገልግሎትን ማጠናከርን ጨምሮ አሳሳቢ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል ያለውን 1.8 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጥ የጃፓን መንግስት አሳውቋል።

በዚህም የገንዘብ ድጋፉ የጃፓን ኤምባሲ እና የአለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች የኮሌራ፣ የኩፍኝ እና የወባ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር ለሚሰሩት ስራ እንዲሁም የተመረጡ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እንደሚውል ተነግሯል።

@TikvahethMagazine