Get Mystery Box with random crypto!

ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ በኦንላይን ተመዝግበው ባሉበት እንዲመጣላቸው የሚያስችል አገልግሎት | TIKVAH-MAGAZINE

ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ በኦንላይን ተመዝግበው ባሉበት እንዲመጣላቸው የሚያስችል አገልግሎት ተጀመረ

ብሔራዊ መታወቂያ ካርድን በኦንላይን ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ካሉበት ሆነው በማዘዝ ባሉበት የማድረስ ሥራ መጀመሩን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ማስታወቁን ኢፕድ ዘግቧል።

የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ የሕትመት ሥራ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ሲከናወን የቆየ ሲሆን የብሔራዊ መታወቂያ ካርዱን ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎችም አገልግሎቱን ለማግኘት በአካል መገኘት ይኖርባቸው ነበር። አሁን ግን ዜጎች አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ የኦንላይን ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን የክፍያ ሥርዓቱም በቴሌ ብር እና በባንክ መክፈል እንደሚቻል ተጠቁሟል።

የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች card-order.fayda.et ድረ ገጽ ላይ በኦንላይን መመዝገብ እንደሚችሉ ሲገለፅ ፥ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ባሉበት ቦታ እንዲመጣላቸው ማዘዝ ይችላሉ ተብሏል። ዜጎች ምዝገባ ከማድረጋቸው በፊት የፋይዳ ቁጥራቸውን የሚገልጽ የጽሑፍ መልዕክት በስልካቸው ስለመላኩ ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸውም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine