Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት በ8 ወር ውስጥ ከ150 ሺ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ መላኳ ተነገረ | TIKVAH-MAGAZINE

ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት በ8 ወር ውስጥ ከ150 ሺ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ መላኳ ተነገረ

ኢትዮጵያ በተያዘው 2016 በጀት ዓመት በ8 ወር ውስጥ ከ150 ሺ ቶን በላይ ቡና ወደ ተለያዩ ሀገራት መላኳን ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ሰምቻለሁ በማለት ሀገሬ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በዚህም 716 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ማህበሩ የገለፀ ሲሆን ማህበሩ የኮንትሮባንድ ችግሮች፤ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና በቀይ ባህር ላይ የሚስተዋለው ችግር ተግዳሮት እየሆነበት እንደሚገኝ ጠቁሟል።

@TikvahethMagazine