Get Mystery Box with random crypto!

የአምስት ዓመቷን ታዳጊ ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው ወጣት #በ6ወር እስራት እንዲቀ | TIKVAH-MAGAZINE

የአምስት ዓመቷን ታዳጊ ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው ወጣት #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ የአምስት ዓመቷን ታዳጊ ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰውን የ17 ዓመት ወጣት #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ የወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን የወምበራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ዕለተ ዓርብ ታህሳስ 26/2016 ዓ/ም በደብረ―ዘይት ከተማ 02 ቀበሌ ሲሆን በተለምዶ ሳንቂ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 10 ሰዓት ገዳማ የአምስት ዓመቷን ህፃን አስገድዶ የመድፈር ድርጊት ከፈፀመ በኃላ በመኖሪያ ቤቱ መያዙ ተገልጿል።

የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት ከወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት የተላከለትን በቂ የሰውና የህክምና እንዲሁም የዐቃቢ ህግ ማስረጃዎችን በማረጋገጥ የምርመራ ስራ ሲያከናውን ቆይቶ ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት ውሳኔ አስተላልፎበታል።

በዚህም መሠረት የወረዳው ፍርድ ቤት መጋቢት 09/2016 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ወጣት #የ6ወር እስራት እንደተበየነበት የወምበራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የፍርድ ቤቱን የወንጀል ችሎት ዋቢ በማድረግ #በደብዳቤ በላከው መረጃ መጥቀሱ ተገልጿል።

መረጃው የመተከል ዞን የወምበራ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

@TikvahethMagazine