Get Mystery Box with random crypto!

በጓደኛዋ ግፊት የቤተሰቦቿን ንብረት የሰረቀችው ተጠርጣሪ ድርጊቱ የተፈጸመው የካቲት 14 በድሬዳዋ | TIKVAH-MAGAZINE

በጓደኛዋ ግፊት የቤተሰቦቿን ንብረት የሰረቀችው ተጠርጣሪ

ድርጊቱ የተፈጸመው የካቲት 14 በድሬዳዋ ከተማ በወረዳ 4 ልዩ ስሙ መብራት ሀይል አዩቤ ጋራዥ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው፥ ተከሳሽ በአንድ ትምህርት ቤት የሚማሩ ሶስት ጓደኞቿን ከቤተሰቦቻቸው ላይ ያላቸውን ንብረት እንዲዘርፉ በመንገር የዘረፉትንም ንብረት ሸጠው ከተማ ቀይረው የራሳቸውን የተሻለ ህይወት እንደሚኖሩ ታሳምናለች።

በዚህ ሀሳብ የተስማማችው ሌላኛዋ ተጠርጣሪ ከቤት እንደደረሰች በሳጥን ውስጥ ተቀምጦ የነበረውን የዋጋ ግምታቸው ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የወርቅ እና ብር ጌጣጌጥ እናታቸውን አጥተው ቤተሰቦቿ በሀዘን በነበሩበት ወቅት ሰርቃ ወደ ጓደኛዋ ታመራለች።

ይህን የተመለከተችው ወንጀሉን የጠነሰሰችው ግለሰብ በፍጥነት ለደላሎች ተናግራ በማሸጥ ወርቁን ሰርቃ ያመጣችው ተከሳሽ ግለሰብ ከሁለት ጓደኞቿ ጋር አያይዛ ወደ ሀረር ከተማ ትልካቸዋለች።

የስርቆት ወንጀሉ የተፈፀመባቸው ቤተሰቦች ጉዳዩን ለፖሊስ ሲያደርሱም የሰማሁት ነገር የለም ብላ ክዳ የነበር ቢሆንም በኋላ ላይ እራሷን ታማኝ እና አዛኝ በማስመሰል የት እንደሚገኙ ትናገራለች።

ከዚያም፥ የገንደ ቆሬ ፖሊስ ጣቢያ ያደራጀው የምርመራ ቡድኑን ከሀረሪ ፖሊስ ጋር በመነጋገር ባደረገው ብርቱ ክትትል ተጠርጣሪዎችን በሀረር ከተማ ከሚገኘው ጭፈራ ቤት ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።

በተጨማሪም፥ የተለያዩ የምርመራ እና ክትትል ስራዎችን በመስራት ንብረቱን ያሸጡ ደላሎችንም በመያዝ ከተሸጠበት ቦታ ንብረቶቹን ማሰባሰብ መቻሉን ዋና ሳጅን ስንዱ ካሳሁን ተናግረዋል።

በአሁኑ  ወቅት ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ከድሬ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@TikvahethMagazine