Get Mystery Box with random crypto!

የካፒታል ገበያ በተዓማኒነት እንዲሁም በብቃት እንዲንቀሳቀስ ይረዳል የተባለ ስምነት ተደረገ የኢት | TIKVAH-MAGAZINE

የካፒታል ገበያ በተዓማኒነት እንዲሁም በብቃት እንዲንቀሳቀስ ይረዳል የተባለ ስምነት ተደረገ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያውን በተዓማኒነት እንዲሁም በብቃት እንዲንቀሳቀስ ይረዳል ያለውን 2 ስምምነት ከተለያዩ ተቋማት ጋር መፈራረሙን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

የመጀመሪያው ስምምነት “የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተዐማኒነት ግብረ ኃይል የትብብርና ቅንጅት የመግባቢያ ስምምነት ቁ. 01/2016" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ስምምነቱ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣  እንዲሁም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መካከል ተደርጓል።

የስምምነቱ ዓላማ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ህጋዊ እና ከወንጀል ድርጊቶች የጸዳ ለማድረግ በተቋማቱ መካከል ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ የሕግ ማስከበር ስርዐት በመፍጠር የካፒታል ገበያውን ተዐማኒነት ማረጋገጥ ነው ተብሏል።

ሁለተኛው ስምምነት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተደረገ የትብብር ስምምነት ሲሆን ስምምነቱ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አጀንሲ፣ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት መካከል የተደረገ ስምምነት መሆኑ ተገልጿል።

ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ የቴከኖሎጂ ድጋፎችን ያካተተው ይህ ስምምነት የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱን የገበያ መቆጣጠር እና የኢንቨስተሮችን ደህንነት የመጠበቅ አቅሙን ለማሳደግ ያለመና መዋቅራዊ የአደጋ ስጋቶችን የመቀነስ አላማን በቀጥታ መደገፍ የሚያስችል እንደሆነ ነው የተገለፀው።

#TikvahEthiopia

@TikvahethMagazine