Get Mystery Box with random crypto!

በማጂ ወረዳ በዛሬው ዕለት በደረሰ የመብረቅ አደጋ የ1 ሰው ህይወት አለፈ። በደቡብ ምዕራብ ህዝቦ | TIKVAH-MAGAZINE

በማጂ ወረዳ በዛሬው ዕለት በደረሰ የመብረቅ አደጋ የ1 ሰው ህይወት አለፈ።

በደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል፤ ምዕራብ ኦሞ ዞን ማጂ ወረዳ ችግት ቀበሌ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7:00 አካባቢ በደረሰ የመብረቅ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

በአደጋውም፥ ከብቶችን በመጠበቅ ላይ የነበሩ በ60ዎቹ ዕድሜ ክልል የሚገኙ አዛውንት ህይወት ያለፈ ሲሆን በወቅቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመዝነብ ላይ እንደነበር ነው የተገለጸው።

አዛውንቱ በእርሻ ማሳቸው አቅራቢያ በሚገኝ ጎጆ ውስጥ ተጠልልው ባሉበት ወቅት በደረሰ የመብረቅ አደጋ ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን ወረዳው አስታውቋል።

በተመሳሳይ በወረዳው መጋቢት 9 ቀን ከርሲ ቀበሌ አባት እና ልጅ ከብት እየጠበቁ፤ ዛፍ ስር ተጠልለው ባሉበት ወቅት ከአባቱ ጋር የነበረው የ16 ዓመት ታዳጊ በደረሰ የመብረቅ አደጋ ወዲያው ህይወቱ ማለፉን ወረዳው ገልጾ ነበር።

@tikvahethmagazine