Get Mystery Box with random crypto!

በሉሜ ወረዳ ልዩ ስሙ ጎዴ ዮሐንስ በተባለ አካባቢ የደረሰው አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ! ከአረርቲ ከ | TIKVAH-MAGAZINE

በሉሜ ወረዳ ልዩ ስሙ ጎዴ ዮሐንስ በተባለ አካባቢ የደረሰው አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ!

ከአረርቲ ከተማ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ተጓዦች በሉሜ ወረዳ ልዩ ስሙ ጎዴ ዮሐንስ በተባለ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ11 ተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

አደጋው አይሩፍ የኮድ ቁጥር ኦሮ 27600 የሆነ መኪና ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ ሴራሚክ ጭኖ ከቆመ መኪና ጋር በመጋጨቱ የተከሰተ መሆኑን የአረርቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸው ለማ በሰጡት የሀዘን መግለጫ ገልጸዋል።

የሉሜ ወረዳ ኮሚኒኬሽን በበኩሉ አደጋው ጠዋት 11:30 ላይ መከሰቱን ጠቅሶ ወደ አዳማ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከቆመ IVCO TRAKAR-ET 48435 ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን ገልጿል።

በአደጋውም የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 2ቱ ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሷል። በተጨማሪም በሁለት ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንዲሁም በአንድ ሰው ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን ነው የገለጸው።

የሉሜ ወረዳ የትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ተክልየ ታምሩ የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እንደሆነ ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine