Get Mystery Box with random crypto!

ሠላሳ ባለማቀዝቀዣ ኮንቴይነሮችን ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑን ኢባትሎድ ገለጸ። የአት | TIKVAH-MAGAZINE

ሠላሳ ባለማቀዝቀዣ ኮንቴይነሮችን ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑን ኢባትሎድ ገለጸ።

የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በትኩሱ ለውጭ ገበያ የሚያደርሱ ባለማቀዝቀዣ ኮንቴይነሮች /Reefer Containers/ በመጪው ሳምንት መጨረሻ ጅቡቲ ይደርሳሉ ሲል የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል።

ባለማቀዝቀዣ ኮንቴይነሮቹ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ እና በቀላሉ ሊበላሹ የሚችሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ መዳረሻቸው እንዲጓጓዙ ለማድረግ የተገዙ ናቸው ተብሏል።

በ9መቶ 76ሺ 5መቶ የአሜሪካን ዶላር ከቻይናው Dalian CIMC Special Logistics Equipment Co.,Ltd የተገዙት እነዚህ ሠላሳ ባለ አርባ ጫማ /40 ft/ /ኮንቴይነሮች በጅግጅጋ መርከብ ተጭነው ነው ወደ ጅቡቲ እየመጡ መሆናቸውን ነው ድርጅቱ የገለጸው።

ለእነዚህ ባለማቀዝቀዣ ኮንቴይነሮች ማስተናገጃነት በሞጆ ወደብና ተርሚናል ልዩ ተርሚናል /Reefer Container Terminal/ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ኮንቴይነሮቹ የወጪ ምርቶችን በባቡር በፍጥነት ጅቡቲ ለማድረስ እና በመርከብ ወደ መዳረሻቸው ለማጓጓዝ ብሎም የወጪ ንግድን በመደገፍና በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethmagazine