Get Mystery Box with random crypto!

#SouthOmo_Zone - በደቡብ ኦሞ ዞን እስካሁን ባለው መረጃ ምክንያቱ በውል ባልታወቀ በሽታ | TIKVAH-MAGAZINE

#SouthOmo_Zone

- በደቡብ ኦሞ ዞን እስካሁን ባለው መረጃ ምክንያቱ በውል ባልታወቀ በሽታ በሐመር ወረዳ በሦስት ቀበሌያት ከ4 ሺህ 5 መቶ በላይ በጎችና ፍየሎች ሞተዋል። ቀሪ ሌሎች እንስሳት ላይ አደጋው እንዳይዛመት የዞኑ አስተዳደር ከሪጅናል ላብራቶሪ ጋር በመቀናጀት የክትባት አገልግሎት እንዲሰጥ በመስስማማት እየተሠራ መሆኑን ገልጿል።

- በዞኑ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዝናብ ባለመዝነቡ ከ3 መቶ 37 ሺህ በላይ የማህብረሰብ አካላትና ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ እንስሳት ለድረቅ ተጋላጭ ሆነዋል።

- በአሁኑ ወቅት በአንፃራዊ መልኩ እየጣለ ያለው ዝናብ ጎርፍ አስከትሎ ሌላ ጉዳት እንዳያስከትል ብሎም ደቡብ፣ ሰሜንና ባካ ዳውላ አሪ ወረዳዎች ላይ የመሬት መንሸራተትና ናዳ ሊያስከትል እንደሚችል ተሰግቷል። ለዚህም የወረዳ አመራር አካላት ከወዲሁ መፍትሄው ዙሪያ እንዲሰሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- የብሄራዊ ሜቲዮሮሎጂ ትንበያ የዝናቡ መጠን ጠንከር ባለ መልኩ በዞኑ እንደሚቀጥል ይጠቁሟል።

- በዞኑ ናፀማይ ወረዳ ሉቃ ቀበሌ ምሽት ላይ በተከሰተ ጎርፍ እስከአሁን 7 መቶ ማህብረሰብ አካላት መፈናቀላቸውንና ከ250 በላይ እንስሳት መሞታቸው ተገልጿል።

- ለተፈናቃዮቹ አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቁት ተጎጂዎች ጎርፉ ለውሃ ወለድና መሰል የጤና ችግር ሊያስከትል ስለሚችል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ድጋፍ እንዲደረግ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

Credit : የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት

@tikvahethmagazine