Get Mystery Box with random crypto!

'የኢትዮጵያ ክላሲካል ሙዚቃዎች እናት' 'የኢትዮጵያ ክላሲካል ሙዚቃዎች እናት' ተብለው የሚጠሩት | TIKVAH-MAGAZINE

"የኢትዮጵያ ክላሲካል ሙዚቃዎች እናት"

"የኢትዮጵያ ክላሲካል ሙዚቃዎች እናት" ተብለው የሚጠሩት እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ በ100 ዓመታቸው ማረፋቸውን የሀገር ውስጥ የዜና ተቋማት ዘግበዋል።

እማሆይ ፅጌ ማርያም ከአባታቸው ከከንቲባ ገብሩ ደስታና ከእናታቸው ከወ/ሮ ካሳየ የሌምቱ በአዲስ አበባ ከተማ በ1915 ዓ.ም ታህሳስ 4 ቀን ነው የተወለዱት።

በስድስት ዓመታቸው በኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ከታላቅ እህታቸው ስንዱ ገብሩ ጋር ለትምህርት ወደ ስዊዘርላንድ የተጓዙ ሲሆን መሠረታዊ ትምህርት፣ ቋንቋ እና ሙዚቃ አጥንተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር መዋቅር ሲዘረጋም የመጀመሪያዋ ሴት ፀሐፊ በመሆን ለ2 ዓመት አገልግለዋል።

ለዕረፍት ብለው ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ባቀኑበት በ25 ዓመታቸው በመመንኮስ ለአስር አመታት እዛው የቆዩ ሲሆን በኋላ ላይም ወደ አባታቸው ሀገር ጎንደር በመሄድ ለአምስት አመታት ቆይተዋል።

ከዛም ከእናታቸው ጋር በመሆን ወደ እየሩሳሌም የሄዱ ሲሆን እናታቸው ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ሲመለሱ እማሆይ ግን በጳጳሱ በአቡነ ዮሴፍ ፅ/ቤት ለአምስት አመታት አገልግለዋል። በዚህ መሀልም መነኩሴ ሁነው እንዴት ፒያኖ ይጫወታሉ በሚል አለመግባባት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። የንጉሱ አገዛዝ በወታደራዊ አገዛዝ ሲተካ ዳግም ወደ እስራኤል ተመልሰዋል።

ከሰሯቸው በርካታ ስራዎች መካከልም Homeless Wonder (ሆምለስ ወንደር)፣ The son of seam (ዘ ሰን ኦፍ ሲም)፣ The mad man's daughter (ዘ ማድ ማንስ ዶተር) እና Mother's love (ማዘርስ ላቭ) የሚል አርዕስት ያላቸው ሥራዎች በምሳሌነት ይጠቀሳሉ።

እማሆይ ጽጌ ማርያም እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ዕብራይስጥኛ፣ አማርኛና ግዕዝን አቀላጥፈው ይናገሩ ነበር። የተለያዩ የሙዚቃ ስራዎቻቸውንም በተለያዩ ኮንሰርቶች ላይ በማቅረብ የሚገኘውንም ገንዘብ ለድሆች መርጃ አውለዋል።

ከእረፍታቸው ጋር ተያይዞ ዝርዝር መረጃ ለጊዜው አልወጣም።

@tikvahethmagazine