Get Mystery Box with random crypto!

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን አገልግሎት መቆራረጥ ቅሬታን አስ | TIKVAH-MAGAZINE

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን አገልግሎት መቆራረጥ ቅሬታን አስነስቷል።

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሆስፒታሉ ከሚሰጡ ህክምናዎች አንዱ በሆነው የካንሰር ህክምና ማዕከል ያለው የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን በመቆራረጡ ምክንያት ብዙ ወረፋ ጠብቀው አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ ታካሚዎች እየተንገላቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በካንሰር ህክምና ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ደግሞ በማሽኑ አገልግሎት መቋረጥ ሳቢያ ብዙ ወራትን ወረፋ ጠብቀው አገልግሎቱን ለማግኘት የሚመጡ ታካሚዎችን ህይወት አደጋ ላይ መውደቁንና በባለሙያዎችም ላይ የስነ ልቦና ጫና መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡

የህክምና ማዕከሉ ኃላፊ የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ኤዶም ሰይፈ የማሽኑ አገልግሎት ሲቋረጥ የታካሚዎቹ ህመም ይበልጥ ሊወሳሰብ የሚችልበት አጋጣሚ ስለመኖሩ ገልጸዋል፡፡

ለማሽኑ ጥገና የሚስፈልጉ መለዋወጫዎች በቶሎ አለመገኘታቸውና አለመድረሳቸው ለአገልግሎቱ መቆራረጥ ዋና መንስኤ ነው ያሉት ኃላፊዋ አንድ ማሽን በቂ ባለመሆኑ ህሙማንን መታደግ ይቻል ዘንድ ተጨማሪ ማሽን ሆስፒታሉ እንደሚያስፈልገው መጠቆማቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

#ማስታወሻ፡ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን አገልግሎት መስጠት ያቆመው ባለፈው ሳምንት ሲሆን ከሁለት ቀናት በኋላ አገልግሎት አገልግሎት መስጠት #መጀመሩን ማረጋገጥ ችለናል።

በዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ በየአመቱ 70 ሺህ ሰዎች በካንሰር ይያዛሉ።

በሌላ በኩል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውንና ጨረር በማመንጨት ካንሰርን የሚገድለውን ‹‹ሌይነር አክስለሬተር›› የተሰኘ ዘመናዊ የካንሰር ህክምና መስጫ ማሽን በ24 ሚሊየን ዶላር ወጪ ለ7 ዩንቨርስቲዎች ያስረከበ ቢሆንም አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የጅማና የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው።

@tikvahethmagazine