Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ከሚመረተው ኤሌክትሪክ ኃይል አብዛኛው ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም፤ ምክንያቱ ምን ይሆን | TIKVAH-MAGAZINE

በኢትዮጵያ ከሚመረተው ኤሌክትሪክ ኃይል አብዛኛው ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም፤ ምክንያቱ ምን ይሆን?

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የማመንጨት አቅሟ ከ5 ሺህ 200 ሜጋ ዋት በላይ የደረሰ ቢሆንም እየተጠቀመች ያለው የኃይል አቅርቦት ግን ከ 1 ሺህ 700 ሜጋ ዋት የዘለለ አይደለም።

የሚመነጨውን ኃይል መሸከም የሚችልና ወደ እያንዳንዱ ደንበኛ የሚያደርስ መሠረተ ልማት አለመዘርጋቱ የምታመነጨውን ኤሌክትሪክ ኃይል እንዳትጠቀም አድርጓታል ነው የተባለው።

ይህን የገለጹት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ሲሆኑ የችግሩ መንስኤም ኃይል ለማመንጨት የሚሰጠውን ትኩረት ያህል ኃይልን ተደራሽ ለማድረግ የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቂ ኃይል እያመነጨ ቢሆንም የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያዎች ቁጥር ግንባታ አነስተኛ በመሆኑ ተደራሽነቱ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛልም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እርቀው የሚገኙ አካባቢዎችን ተደራሽ ለማድረግ የፀሐይ የኃይል ምንጭን እንደአማራጭ እየተጠቀመ መሆኑን ገልጸው በዚህም በ12 የገጠር ከተሞች በ8.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የፀሐይ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አቶ መላኩ አንስተዋል። (EPA)

@tikvahethmagazine