Get Mystery Box with random crypto!

'ነጭ ወርቅ' የተባለው እጣን በኩንታል እስከ 23 ሺ ብር ያወጣል! ምዕራብ ጎንደር ዞን አጠቃላይ | TIKVAH-MAGAZINE

"ነጭ ወርቅ" የተባለው እጣን በኩንታል እስከ 23 ሺ ብር ያወጣል!

ምዕራብ ጎንደር ዞን አጠቃላይ ካለው የደን ሽፋን 30 በመቶው በእጣን ዛፍ የተሸፈነ ነው። በእጣንና ሙጫ በማምረት የተሰማሩ ሰዎች ከዚሁ ምርት የሚገኘው ገቢ ከሰሊጥ፣ ጥጥና ማሽላ ምርት ከሚገኘው ገቢ በአስር እጥፍ  ብልጫ እንዳለው ያስረዳሉ።

የኑስ ዲቦ የተባሉ አምራች በ2014 ዓ.ም 1 ኩንታል እስከ 23 ሺህ ብር ለገበያ ማቅረብ መቻሉን ለአብነት አንስተዋል። በዚህም የአብዛኛው የማኅበሩን አባላት  ሕይወት መለወጡን ነው የገለጹት።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፦

- በ2014 በጀት ዓመት በዞኑ 4 ሺህ 80ዐ  ኩንታል የሚጠጋ እጣንና ሙጫ የተመረተ ሲሆን ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ  ደግሞ ገቢ ተገኝቷል።

- ዘንድሮ ከ9 ሺህ ኩንታል በላይ የእጣንና ሙጫ ምርት በመሰብሰብ ከ163 ሚሊዮን ብር በላይ  ደግሞ ገቢ ለማግኘት ታቅዷል።

- በዞኑ ያለውን ሃብት በሙሉ አቅም ማምረት ቢቻል በዓመት ከ35 ሺህ በላይ ኩንታል የእጣንና  ሙጫ ምርት ማግኘት የሚቻለሰ ሲሆን ይህም አሁን ባለው ዋጋ እንኳ ለገበያ ቢቀርብ 609 ሚሊዮን ብር ዞኑ ገቢ ማግኘት ይችላል።

ይህ ኃብት ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በሚጠበቀው ልክ ጥቅም ላይ አልዋለም። አሁን ላይ በአከባቢው 22 ማኅበራትና 24 ባለሃብቶች በእጣንና ሙጫ ማምረት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል።

የሕገ ወጥ እርሻ መስፋፋት፣ ሰደድ እሳት እና ሌሎች ችግሮችን ለመከላከል የጥበቃ ሥራ ላይ ትኩረት መደረጉ የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋጋው እየጨመረ በመምጣቱ የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥበቃ እየተጠናከረ  መምጣቱ ተነግሯል።

ምንጭ : አሚኮ

@tikvahethmagazine