Get Mystery Box with random crypto!

'በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ በ2022 43,000 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፤ ግማሾቹ ከ5 ዓመት በታች | TIKVAH-MAGAZINE

"በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ በ2022 43,000 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፤ ግማሾቹ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት ናቸው" - ተ.መ.ድ

በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ ተከታይ 5 የዝናብ ወቅቶች መቋረጥ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ 43,000 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን አዲስ የወጣው የተመድ ሪፖርት ያሳናል።

ከሟቾቹ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት መሆናቸውን ነው የተጠቀሰው። እስከ ተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት [2023] አጋማሽም ሀገሪቱ ከ18,100 - 34,200 ዜጎቿን በድርቅ ምክንያት እንደምታጣ ተገምቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በሶማሊያ አምስት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች በማለፋቸው አምስት ሚሊዮን ሰዎች ለአስከፊ የምግብ እጥረት እንዲሁም ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋላጭ ሆነዋል።

@tikvahethmagazine