Get Mystery Box with random crypto!

' ለህንጻ ግንባታ የተቆፈረ አፈር ተንዶ የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል ' - የእሳትና አደጋ ስጋት ስ | TIKVAH-MAGAZINE

" ለህንጻ ግንባታ የተቆፈረ አፈር ተንዶ የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል " - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ፣ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ለህንጻ ግንባታ መሰረት የተቆፈረ አፈር ተንዶ የሁለት ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ሕይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ አደጋው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8:59 ላይ ልዩ ቦታው " መነን ሰፈር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መከሰቱን ገልጿል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እንዲሁም ከጸጥታ አካላትጋር በመተባበር የሟቶችን አስከሬን ማውጣት እንደቻሉ ኮሚሽኑ አመልክቷል።

ኮሚሽኑ በመዲናዋ በግንባታ ስራዎች ላይ መሰል ተደጋጋሚ አደጋዎች እየተከሰቱ በመሆኑ አሰሪዎችና ሰራተኞች አስፈላጊውን የደህንነት መስፈርት ጠብቀው እንዲሰሩ አሳስቧል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia